ሰልጣኝ
አሜን ሙያ ማሰልጠኛ ስልጠና ከመጀመሬ በፊት በረዳትነት የተወሰነ የሠራሁ ቢሆንም የኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታን ኢንጅነሪንግ በአግባቡ ለመረዳት ተቸግሬ ነበር። የኢንስቲዩቱ ስልጠና አጭርና ማንም ሰው ሊረዳው የሚችለው ከመሆኑም በላይ በተግባር የታገዘ ስለሆነ ከስልጠናው በኋላ በልበ ሙሉነት መሥራት አስችሎኛል። በድርጅቱ በረዳትነት የሥራ ዕድል አግኝቶ ከመሥራት ጀምሮ አሁን በሙሉ ባለሙያነት በመሥራት ላይ እገኛለሁ። ጥሩ የገቢ ምንጭም ሆኖኛል።
ሰልጣኝ
የአሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ ነበርኩ አሁን ብዙ ለውጥ አምጥቻለሁ ተቋሙ ላይ ባገኘሁት ክህሎትና ልምድ በግሌ ኢንስታሌሽን እየሰራው ነው ሌሎቻችሁም ይህን ስልጠና ወስዳችው ወደስራ ብትገቡ ብየ እመክራችዋለው። አመሰግናለሁ አሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ
ሰልጣኝ
አሜን በመማሬ በጣም እድለኛ ሆኛለሁ ከአንዴም ሦሦት ጊዜ ድርጅቶች ላይ እንድሰራ ዕድል አመቻችቶልኛል በአጭር ጊዜ ውስጥ ብቁ አርጎኛል ማረጋገጫም ሰጥቶኛል። የሙያ ባለቤት ለመሆን ወሳኝ ኢንስቲትዩት ነው።
ሰልጣኝ
አቤኔዘር አበራ እባላለው የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተመራቂ ነኝ በአሜን ቴ/ኢ በBuilding Electrical Installation ሙያ የተግባር ስልጠና መውሰዴ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ ያላገኘውትን ለስራው አለም የሚያበቃ የተግባር ልምድ እንዳገኝ አስችሎኛል በተጨማሪም ተቋሙ ባመቻቸልኝ የስራ እድል አማካኝነት በስራ ላይ እገኛለው ብዙዎችም የዚ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል ገበያው ላይ ከልማድ አሰራር የወጣ በእውቀት ላይ የተመሰረ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ እንዲበዛ ለምታደርጉት አስተዋፆ ላመሰግን ወዳለው